የኢዜማ የመሬት ወረራ ጥናት ተዓማኒነት

Published by Ayele Gelan on

[originally published by Reporter Amharic, Ethiopian Weekly Newspaper, 23 September 2020]

ኢዜማዎች በቅርቡ የአዲስ አበባ መሬት ወረራን በተመለከተ አደረግን ያሉትን ባለ 13 ገጽ የጥናት ጽፍ ይፋ ማድረጋቸው ታወሳል። ከሁሉ በፊት ጥናት ላይ ተመረተው የውሳኔ ሳብም ሆነ ትችት ለማቅረብ ጥረት በማድረጋቸው፣ ኢዜማዎች ምጋና ይገባቸዋል። ሊበረታታ የሚገባ ባህል ነው። 

እንኳንስ በተቃዋሚ ፓርቲ ደረጃ መንግትም ቢሆን መረጃ ላይ የተመረተ ውሳኔ የመስጠት ባህል በገራችን አልዳበረም:: በሚያሳዝን ደረጃ ትልቅ ፖለቲካዊና ኮኖሚያዊ ውሳኔዎች፣ ምንም ጥናትና መረጃ ላይ ሳይመረቱ እንዲሁ በዘፈቀደ ሲተላለፉ እያየን ቆሽታችን እያረረ እንኖራለን። ምናልባት ከዚህ በኋላ ሌሎች አካላት ኢዜማ የቀደደውን ፈር ተከትለው፣ ለመረጃ ቦታ የመስጠት ባህል (Evidence-Based Decision-Making) እየዳበረ ይሄዳል ብዬ ተስፋ አደርጋሁ።

ይህን ካልኩ በኋላ በኢዜማ ጥናት ላይ ያለኝን አስተያየት ወደ መስጠት አመራለሁ። አስተያየቴን የምሰጠው የጥናቱ ጭብጥ የሆነው የመሬት ወረራ የተተረጎመበት መንገድ ላይና ይኼ ደግሞ የጥናቱን ውጤት ተዓነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ነው።

የኢዜማ ጥናት ሪፖርት ትኩረቱ የአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ፣ “የመሬት ወረራ”ን ደግሞ ጠበብ ያለ ትርጉም በመስጠት ይጀምራል። አጥው ቡድን ወደ ጥናቱ የተማራው ‹‹የመሬት ወረራ ማንኛውንም የሕዝብ/የመንግሥት የሆነ መሬትን ከሕግ ውጪ በሆነ አግባብ በግለሰብ ወይም በቡድን የመያዝ ተግባር ነው፤›› (ገጽ 2)። የኢዜማ ጥናት ችር ከዚህ ነው የሚጀምረው።  ማንኛውንም የግል የሆነ መሬት አላግባብ ቢወረስ አያገባንም የሚሉ ይመስላል። ይህ ደግሞ ለዜነት መብት ጠበቃ ቆሜያለሁ ክሚል የፖለቲካ ቡድን አቋም ጋር ይቃረናል።

አንድ ላፊነት የሚሰማው፣ ለወደፊት ገር ለማስተዳደር በጩነት ለመቅረብ እየተዘጋጅሁ ነው የሚል ገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ይቅርና፣ ማንም ኢትዮጵያዊ ከዳር እስከ መል ገር ያለ ነዋሪ ዜጋ፣ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሀቅ አለ። ይህም የአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ሲባል ትልቁ፣ አንጋፋውና ዘግናኙ የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች ከአባቶቻቸውና ቅድመ አያቶቻቸው መሬት በገፍ የተፈናቀሉበትና ለጎዳና ተዳዳሪት የተዳረጉበት ደት ነው። ይህ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን፣ የዓለም ተራማጅ ኃይሎች ሁሉ ያስደነገጠ ክስተት ነው።

ሌቦች ዘረፋ አካሂደው ግለሰቦችን ካራቆቱ በኋላ የዘረፉትን ሀብት በመከፋፈል ደት ላይ በመካከላቸው አለመግባባት መፈጠር ብዙም አያስገርም፣ የተለመደ ነው። በዚህ ደት ደግሞ፣ ከሌቦቹ መካከል ብልጣ ብልጡና ጉልበተኛው ሌሎቹን ቀማኞች ሸውዶ፣ አብረው ከሰረቁት ሀብት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። የኢዜማ ጥናት ትኩረት ዋናውን ዘረፋ ወደ ጎን በመተው፣ በሌብነት የተገኘን ብት በመከፋፈል ደት ውስጥ እየተከሰተ ያለ ውዝግብ ላይ ያተኩራል።

መልስ ሊያገኝ የሚገባው ዋናው ጥያቄ፣ ‹‹ኢዜማ ግዙፉን ወንጀል ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ጥቃን ወንጀሎች መመርመርን የመረጠበት ሚስር ምንድነው?›› የሚለው ነው። እውነቱን ለመናገር የኢዜማን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምንነት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ፍንጭ ላው ሰው፣ የሆነው ነገር ብዙም አይገርመውም። በግልጽ ለዝብ ይፋ የሆነ የኮኖሚ ፖሊሲያቸውን አላየሁም፣ ግን አልፎ አልፎ የሚሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እሰማለሁ። ከነዚህ የምረዳው ወደ ገበያ መር (Laissez-Faireየተጠጋ ፖሊሲ የመከተል አዝማሚያ ይታይባቸዋል። ኢዜማ የቅንጅት በኩር ልጅ እንደሆነ ይታወቃል። ቅንጅት ደግሞ ስለመሬት ይዞታ ምን ዓይነት የፖሊሲ አቋም እንደነበው እናስታውሳለን። ቀጥሎም ቅንጅት ይከተል የነበረውን የመሬት ይዞታ ለመከተል ምን ዓይነት ታሪካዊ ሁኔታዎች ከበስተጀርባው እንዳሉም መገንዘብ አዳጋች አይደለም። 

አንድ የፋና ቴሌቪን ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ዴሴምበር 30 ቀን 2019 ባስተላለፈው ፕሮግራም፣ ለኢዜማ መሪ ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። ‹‹ኢዜማ በፊት ቅንጅት ያካሄድ ከነበረው የመሬት ይዞታ የተለየ ወይም ተመሳሳይ ፖሊሲ አለው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ዶ/ር ብርሃኑ የተድበሰበሰ መልስ ነበር የሰጠው። ስለመሬት ይዞታ የነበረው ምልልስ ለመከታተል፣ ይህን ቪዲዮ (https://www.youtube.com/watch?v=zwFOxk2fSCo) ይጫኑና ከ42፡00 ደቂቃ ጀምሮ ይከታተሉ። በአጭሩ የዶ/ር ብርሃኑ መልስ፣ ለባለሀብቶች ኢንቨስትንት ዕድል ለመክፈት ሲባል የአርሶ አደሮች መፈናቀል በኮኖሚ ድገት ደት ውስጥ አቀሬ ክስተት ነው የሚል ነበር።

ከአዲስ አበባ አካባቢ አርሶ አደሮች መፈናቀል ጋር ያለውን ሰቆቃ በሚመለከት ኢዜማ ያለው አቋም ደግሞ፣ ከአጠቃላይ የድርጅቱ የመሬት ይዞታ ፖሊሲ ጠጠርና ጠንከር ያለ ነው። ምክንያቱም አዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች መፈናቀል፣ ከተፈናቀለው ዝብ፣ ማንነትና ባህል ጋር እንዲሁም የመፈናቀሉ ክስተት ያለፉት ጥቂት አርተ መታት ውጤት ብቻ ሳይሆን ለምተ መታት የዘለቀ፣ ከኢትዮጵያ ኤምፓየር አመሠራረት ጋር የሚዛመድና ጭካኔ የተላበት ታሪካዊ ደት ስለሆነ ነው። 

ይህ እንግዲህ ኢዜማ ራችን ብለው የመሬት ዘረፋዎች ሁሉ እናት የሆነውን አዲስ አበባ ዙሪያ መንግት አርሶ አደሮችን ያፈናቀለበትን ክስተት ወደ ጎን የተበትን ምክንያት ይገልጽልናል። ኢዜማዎች ማምለጫ አላቸው ለዚህ፡፡ ቀድሞውንም መሬት የመንግሥት ነው የሚል (ላይ ያለው ቪዲዮ ውስጥ እንደተብራራው)፡፡ ነገር ግን እነሱ ዝርፊያ ነው ብለው የሚወተውቱት ክፍት ቦታዎችና ኮንዶሚኒየሞችም እኮ በመንግት አካላት ነው የተዘረፉት፣ የታችኛው መንግሥት አካል መሆኑ ላይ ነው እንጂ ልዩነቱ!

ኢዜማ ወደ አዲስ አበባ የተጠቃለለውን መሬት እንደ ዘረፋ ያልቆጠረው፣ መሬቱ የተዘረፈው ከኦሮሞ አርሶ አደሮች በመሆኑና የኦሮሞ መሬት የሚባል ነገር ስለማይዋጥለት ነው። የኦሮሞ ምሁራንና አክቲቪስቶች ይህን የመሬት ዘረፋ እንደ ተራ የኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የአዲስ አበባ አካባቢ ኦሮሞን ባህልና ቋንቋ የማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህ ደግሞ ከኢዜማ ርዕዮተ ዓለም ጋር ፊት ለፊት ይጋጫል፡፡ ኢዜማዎች ይህን አካሄድ የዘር ፖለቲካ ብለው ይኮንናሉ። መሬቴን ተቀማሁ፣ ባህሌና ማንነቴም አብሮ እንዲጠፋ ተደረገ ለሚል የኦሮሞ አርሶ አደር ኢዜማዎች ጆሮ እንሌላቸው እንገነዘባለን።

የኢዜማ አጥኚ ቡድን ራችን ብለው ከጥናታቸው ራዳር ይታ የሰወሩትን የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደር ዕጣ ፈንታ፣ በአስገራሚ ሁኔታ ጥናታቸው መጨረሻ ላይ መልሰው ያመጡታል። ያውም ቀደም ሲል የተፈናቀሉትን የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች ዋና ወራሪ ወንጀለኞች ናቸው ብለው በመፈረጅ ነው፡፡ የኢዜማ ሪፖርት እንዲህ ይላል፣ ‹‹በዋናነት በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች ቦታዎቹ ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን መሬቶች ናቸውና በቂ ካሳ ሳይከፈለን ከቦታችን ተነስተናል የሚሉ ግለሰቦችና ወረራ የተፈመባቸው ቦታዎች አካባቢ ላይ የሚገኙ የክፍለ ከተማና የወረዳ ኃላፊዎችና ፈጻሚዎች ናቸው፡፡››

ይህ የኢዜማ ጥናትና ውጤቱ በጣም ሸፍጠኛ አካድ ከመሆንም አልፎ ይን ያወጣ ፍርደ ገምደልነት ነው። ቀደም ብዬ እንዳልኩት፣ የኢዜማዎች አካሄድ እንዴትና ወዴት እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም። ሆኖም ግን ይህን ያህል የወረዱና በርዕዮተ ዓለማዊ አመለካከታቸው ምክንያት ማየት የተሳናቸው ናቸው ብዬ ገምቼ አላውቅም ነበር። በርዕዮተ ዓለም መታወር ብዛት፣ እንዲህ ፊት ለፊት ያለንና በገሃድ የሚታይን ግልጽ ነገር እንዳያዩ አደረጋቸው። የተቀማውን ባለንብረት የተገላቢጦሽ ወንጀለኛ ሌባ ብለው እስከሚጠሩ ድረስ መሄዳቸው አስነዋሪ ድርጊት ነው።

ጅምሩ ግራ የተጋባ ነገር መጨረሻው አያምርም እንደሚባለው መሆኑ ነው (Wrong Premise, Wrong Conclusion)። የኦሮሞ አርሶ አደሮችን ጉዳይ ገሸሽ ለማድረግ፣ ኢዜማ ሆን ብለው መሬት ወረራን የተጣመመ ትርጉም በመስጠት ጥናታቸውን ጀምረው፣ እንዲህ ዓይነት ትርጉም የለሽ፣ አሳፋሪና ተዓማኒነት የሌለው ውጤት ላይ ደረሱ። ለወደፊቱ ኢዜማዎች ጥናት ሲያካዱም ሆነ ፖሊሲ ሲቀር፣ ይህን ብዥታ የሚፈጥርባቸውን የርዕዮተ ዓለም መነጽር አውልቀው ማየት ቢጀምሩ፣ እውነተኛዋን ኢትዮጵያ የማየት ችሎታቸው እያደር ይዳብር ይሆናል።


Leave a comment:

Your email address will not be published. Required fields are marked *


CAPTCHA Image