የዳንኤል ክብረት ውስጠ ወይራ ንግግር!
እዚህ ቪዲዮ ላይ የምትሰሙት የዳንኤል ንግግር ጭብጥ “የዓላማ ጽናት” ወሳኝነት ነው። ጽናቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ሳትቀየር እንደነበረች ከትውልድ ትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነትን ይመለከታል።
ባንድ መልኩ በጎ አስተሳሰብ ይመስላል፣ የዓላማ ጽናት ተፈላጊ የምሆንበት ጊዜ አለና! የዳንኤል ድስኩር ግን መርዛማ የምሆንበት ምክንያት አለው። ይሀውም ኢትዮጵያ የተለያየ ገጽታ አላት።
ለምሳሌ ዳንኤል መልሶ መላልሶ የሚያንቆለጳጵሳት የድሮዋ ኢትዮጵያ እና የሁላችንንም ማንነት የምታንፀባርቅ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለየቅል ናቸው።
አሁን ያለው የፖለቲካ ፍትጊያ አሮጌዋን ኢትዮጵያ መልሶ ማምጣት በሚፈልጉና አዲሲቷን ኢትዮጵያ ማጠናከር በሚፈልጉ ሃይሎች መካከል ነው።
ሁለቱም የዓላማ ጽናት ያላቸው ይመስላል። በዚህ መልኩ ካየነው የዳንኤል መልክት የድሮዋን ኢትዮጵያ መልሰን ለማምጣት እንትጋ ከማለት የተለየ አይመስለኝም። አንደራደርም እያለ ነው ያለው።
ይህ ደግሞ በጣም አደገኛ መልእክት ነው። በዓላማ ጽናት አስታኮ አክራሪ እና ጽንፈኛ የፖለቲካ አቋም የማራመድ ያህል ነው።
ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት የመቻቻል ፖለቲካ ነው፣ political consensus! ይሄ ደግሞ የማይታረቁ ዓላማዎችን ይዞ በመጽናት ከመዳረቅ ጋር ተቃራኒ ነው።
ስለዚህ የዳንኤል መልእክት በዚህ መልኩ መታየት አለበት። ዳንኤል መደስኮሩን ይከልከል እያልኩ አይደለም፣ የሱን በማር የተላወሰ መርዝ ከመዋጥ እንቆጠብ ማለቴ ነው።