This website uses cookies to improve user experience. If you wish to browse this website without viewing this message, you must agree to accepting our cookie policy which is part of our Privacy Policy. Accept
Privacy & Cookies Policy
Privacy Overview
This website uses cookies to improve your experience while you navigate through the website. Out of these, the cookies that are categorized as necessary are stored on your browser as they are essential for the working of basic functionalities of the website. We also use third-party cookies that help us analyze and understand how you use this website. These cookies will be stored in your browser only with your consent. You also have the option to opt-out of these cookies. But opting out of some of these cookies may affect your browsing experience.
Necessary cookies are absolutely essential for the website to function properly. This category only includes cookies that ensures basic functionalities and security features of the website. These cookies do not store any personal information.
Any cookies that may not be particularly necessary for the website to function and is used specifically to collect user personal data via analytics, ads, other embedded contents are termed as non-necessary cookies. It is mandatory to procure user consent prior to running these cookies on your website.
ኢህኣዴግ ወዴት፡ ክስመት ውይስ ውህደት?
Published by Ayele Gelan on
የዛሬ ሶስት አመት ገደማ፣ አንድ አንጋፋ የህወኣት ባለስልጣን፣ “ኢህኣዴግ ስልጣን የሚለቀው ከሃምሳ አመት በኋላ ነው” ብሎ ነበር። ለምን እስከ ሃምሳ አመት ስልጣን ላይ መቆየታቻው የግድ እንደሆነ ስተነትን እንዲህ ነበር ያለው፡ “የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ አድጎ የቡርዡዋ መደብ ይፈጠራል። ከዚያ የብሄር ፖሎቲካ ያበቃለታል። ያኔ ብሄር ላይ የተመሰረተ የፓርቲ ጥምረት አስፈላጊ አይሆንም። ኢህኣዴግ ይከስምና በመደብ ክፍፍል ላይ የተመሰረተ ፖሎቲካ ቦታውን ይይዛል!” በጣም ደስ የምትል፣ አካሄዷ ግልጽ የሆነች ልብ ወለድ ታሪክ ነበረች። ከሃምሳ አመት በኋላ፣ የነማን ልጆችና ልጅ ልጆች ካፒታሊስቶች ሆነው ሃብታቸዉን ለመጠበቅ ፓርቲ እንደሚመሰርቱ፣ የእነማን ልጆችና ልጅ ልጆች የሰራተኛ መደብ ሆነው ለደመወዝ ጭማሪ ሰልፍ እንደሚወጡ ሁሉ በምናባችን ቁልጭ ብሎ እስክታይ ድረስ የተተነበየች ቆንጆ ልብ ወለድ!
ያቺ ድርሰት ተጽፋ፣ ሃምሳ ይቅርና ግማሽ አመስት አመት እንኳን ሳይሆን፣ በነጎድጓድ የታጀበ ዶፍ ጣለባቸው፣ ያ ህልም በቅጽበት ወደ ቅዠት ተለወጠ። ኢህኣዴግ ከእንቅልፏ ባንና ከተረጋግች በኋላ፣ አሁን ደግሞ ሌላ ትረካ ይዛ ብቅ አለች፡ “አምስት አስርት አመታት ቆይተን ለክስመት መዘጋጀት አስፈላጊ አይደለም፣ እንዲሁ በደፈናው እንወሃድ” የምትል። ለምን መወሃድ አስፈለገ? ለመወሃድስ የሚያስችል በቂ መሰረት አለ ወይ? እና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ያለ አይመስልም። እንዲሁ በደፈናው ውህደት ተባለ።
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የክስመት ልበወለድ ታሪክ የበለጠ ትጥማለች። ቢያንስ ቢያንስ ኪነታዊ ለዛ አላት፣ ታስቃለች። የኋለኛዋ ትርክት ግን በደንብ ለመተረክ እንኳን አትመችም። የጀማሪ ደራሲ ስራ ትመስላለች።
ይሄ የኢህኣዴግ ዉህደት ነገር የሶሻሊሽምን ጽንሰ ሃሳብ መበከልን ተከትሎ የሰው ልጅ የከፈለውን መስዋእትነት አስታወሰኝ። ካርል ማርክስ፣ ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም ለመሸጋገር፣ “የምርት ሃይሎች ጎልብተው እስኪያድጉ መጠበቅ የግድ ነው” ብሎ ነበር። ሌኒን “መጠበቅ አያስፈልግም፣ አቋራጭ መንገድ አለ፣ የሽግግር ጊዜ መድቦ የምርት ሃይሎች እድገት ማፋጠን ይቻላል” አለ። እናም ሌኒን ያለውን ተከተልን። በከፊል ገና ከጋርዮሽ ህብረተሰብ ብቅ እያልን ያለን ሁሉ የሌኒንን መንገድ ሞከርን። ዋጋ ከፈልን! የተከፈለው ዋጋ ምናልባትም ለህብረተሰብ እድገት ቁልፍ የመሆን ተስፋ አዝሎ የነበረው ሶሻሊሽም ከስሮ፣ ተወረወረ፣ ምናልባትም እስከናካቴው!
ላለፉት 28 አመታት ኢህኣዴግ ገዢ ፓርቲ ሆኖ ቆይቷል። በዚህን ጊዜ ሁሉ፣ ቢያንስ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ተቀባይነት ልኖረው የምችልና፣ የኢትዮጵያን መሰተታዊ ችግር ለመፍታት ሲባል የተለያዩ የሀገሪቷን ህዝቦች የሚወክሉ ፓርቲዎችን አቅፎ ነበር። ይህንን ህብረት እውነትም ያሉትን የሀገሪቷን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ሳይሆን፣ ለመሰሪና እኩይ ተግባር ሲጠቀሙበት ቆዩ። የኢህኣዴግ ከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ፣ የነበሩት ልይነቶችና ቅራኔዎች፣ ከሚገባ በላይ እንዲገዝፉ፣ ህዝቦች እንዲጋጩና በያካባቢው ግጭቶችና ፍጥጫዎች እንድሰፍኑ አደረገ። ኢህኣዴግ የዘራቸው ቅራኔዎች፣ የቀመራቸው ሸሮች አድገው ከቁጥጥር ውጪ ሆነው፣ አሁን ሀገሪቷ ለመበታተን ጫፍ ላይ ደርሳ ትታያለች።
በዚህ መካከል እንግዲህ ኢህኣዴግ “ውህደት” የምትለዋን ትረካ ይዛ ብቅ ያለችው። ውህደት ውስጥ የተደበቁ ምስጥሮች እንዳሉ ግልጽ ነው።
1ኛ. የውስጥ ክፍፍልን መደበቅና ማድበስበስ ነው። ህወኣት ጭራሽ በውህደቱ አልታቀፈችም። አዴፓና ኦዴፓ ፍጥጫ ላይ እንዳሉ እናውቃለን። ይህ በንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ የ“ውህደት” ትረካ እየጦዘ ያለው። “ጎረቤት ሆነን መኖር አልቻልንምና እስቲ ደግሞ ቤተሰብ ሆነን እንሞከር፣ በዚያውም ጸባችን እንዳይታወቅብን ለመደበቅ ይመቻል” አይነት ሽንገላ። አይመስልም፣ አያሳምንም! “Dhoksuun fanxoo hin fayyissuu” የምል የኦሮሞ ተረት አለ፣ “በመደባበቅ ከቂጢኝ አይዳንም” እንደ ማለት!
2ኛ. ኢህኣዴግ የርእዮተ አለም ኪሳራ እንደደረሰበት አመነ ማለት ነው። ብሄረሰቦች በጋራ ለመሰረቱት ፌዴራሊዝም ዘብ ቆመናል ስሉን ከረሙ። ፌዴራሊዝሙን ግን ሲያለመልሙት ሳይሆን ሲያቀጭጩት ቆዩ። አሁን በአስራ አንደኛው ሰአት ወደ ህብረ ብሄር ሸርተት ማለት፣ የመሰረቱትን ብሄር ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምን ጥሎ መኮብለል መስሎ ይታየኛል።
3ኛ. ከሁሉ በላይ ይሄኛው ሊሰመርበት ይገባል፤ ኢህኣዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያላወራረዳቸው ብዙ ሂሳቦች አሉዋት። ለውህደት ጥድፊያው እነዚያን በርካታ ወንጀሎች ለማድበስበስ ጭምር ይመስለኛል። ከተጠያቂነት ለመሸሽ!
ስለ ኢህኣዴግ ውህደት ሲነሳ ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ ጉዳዮች ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለባቸው። ህዝብን የሚወክል ፓርቲ ቢኖር፣ እነዚህንና ከዚህ ጠጠር ጠንከር ያሉ ሃሳቦችን አንስቶ ያፋጥጣቸው ነበር። ያንን ቁመና ያለው ቡድን ህገሪቷ እንዳሌላት ይሰማኛል። ስለዚህ መልክቴ ለህዝቡ ነው።
more articles
ECONOMICS OF WALISO TELA BETS
NEBE’s Allocation of Parliamentary Seats to Regional States: Evidence-based?
Maaliif Du’u?
የኢዜማ የመሬት ወረራ ጥናት ተዓማኒነት
How Much Does it Cost to Print Ethiopia’s New Currency Notes?
Turning Crisis into Opportunity
Natti Dhaga’ama, Natti Dhaga’ama!
Ethiopia’s COVID-19 Response Economic Package: Neither Relief nor Stimulus!
ቢያንስ የማርች 8 እለት ወጣት ሴት ድምጿን የማሳማት መብት ሊኖራት ይገባል!
Liqaan Itoophiyaa Saffisaan Tullamee Gaara Guddaa Ta’aa Jira